የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከዞን ግብርና መምሪያ ጋር በመተባበር የአንበጣ መንጋውን ለመከላከልና ማህበረሰቡን ለማስተባበር የቅስቀሳ፣የንቅናቄ ስራዎችን ለማከናወን ወደ ሀራ መስመር ጉዞውን አድርጓል፡፡በቅስቀሳው ሁለት አንቡላንሶች፣የድምፅማጉያ መሣሪያዎችንና ለክልሉ ልዩ ሃይል አባላት መጓጓዣ የሚሆን ሁለቱ አውተብሶችን ይዞ ወደስፍራው ተጉዘዋል፡፡ በዘመቻው የዩኒቨርስቲው አመራሮችም ለሶስተኛ ጊዜ በመከላከል ስራው ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ዩኒቨርሲቲው የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚያስችል አቅም እንዲኖር ለቁሳቁስ ግዥ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍም አድርጓል፡፡ በተጨማሪም የአንበጣ መንጋው ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ ሁለት መኪናዎችን በቋሚነት መድቦ አየሰራም ይገኛል ፡፡
ኮሮናን ሳንዘነጋ በተባበረ ክንድ የአንበጣ መንጋውን በጋራ እንከላከል!መስከረም 28/2012ዓ.ም