ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮዽያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በሚፈቀደ መደበኛ እና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውሉ የቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት የቤተ ሙከራ እቃዎች፤የስነ-ባህሪ ሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች፤የጤና ደሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች፤የመሬት አስተዳደር ትም/ክፍል የቤተ ሙከራ እቃዎች፤የግብርናፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች፤የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች እና የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውን ህጋዊ ተጫራቾች  የመወዳደሪያ ሰነድ ሞልተው እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚቀርብበት ቀንና ቦታ ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሌሎችም መመሪያዎች በጨረታ ማስታወቂያውና በተጫራቾች መመሪያ በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶ በር ዋናዉ ግቢ ፋይናንስና በጀት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 የተጠየቀውን ዋጋ በመክፈል ሰነዱን ገዝተው መውሰድና ሰነዶቹን በወቅቱ ሞልተው እንዲያቀርቡ ዩኒቨርሲቲው በቅድሚያ ያሳስባል፡፡

የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መረጃዎችን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ፡-

  1. የቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት የቤተ ሙከራ እቃዎች ግልጽ ጨረታ ሎት 01/አንድ/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  2. የስነ-ባህሪ ሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተሙከራ ግልጽ ጨረታ ሎት 02/ሁለት/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  3. የጤና ሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች ግልጽ ጨረታ ሎት 03/ሶስት/ የጨረታ መ/ቁ ጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  4. የመሬት አስተዳደር ትም/ክፍል የቤተ ሙከራ እቃዎች ግልጽ ጨረታ ሎት 04/አራት/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  5. የግብርና ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች ግልጽ ጨረታሎት 05/አምስት/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  6. የማህበራዊ ሳይንስና ስን ሰብፋኩሊቲ እቃዎች ግልጽ ጨረታ ሎት 06/ስድስት/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  7. የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ፋኩሊቲ የቤተ ሙከራ እቃዎች ግልጽ ጨረታ ሎት 07/ሰባት/ የጨረታ መ/ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/09/2013
  8. የመካኒካል እና ኬሚካል ምህንድስና ትምህርት ቤት የቋሚ ዕቃዎች ግዥ ዝርዝር Updated