ሴኔቱ በዛሬው ዕለት ከስዓት በፊት በነበረው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳ ከነበሩት መካከል የመምህራን የደረጃ እድገት እና የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎች የጥሪ ሁኔታን የሚመለከቱ ነበሩ። በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በሗላም ውሳኔዎች ተላልፈዋል። ወልድያ ዩኒቨረሲቲ በወራሪው ሃይል ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰበት በሗላ በፍጥነት ወደ መደበኛ ስራው ለመመለስ በተደረገው ጥረት ከነባር የመጀመሪያ አመት ኤክስቴሽንና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በመቀጠል የመጀመሪያ አመት መደበኛ ተማሪዎቹን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችል ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑ በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተማሪዎቹ እንዲጠሩ ውሳኔ ተላልፏል። በመቀጠልም በሁለተኛው አጀንዳ የቀረበውን የመምህራንን የደረጃ እድገት ተመልክቶ አስር መምህራን ከጤና ኮሌጅ፣ አንድ መምህር ከግብርና ኮሌጅ በጥቅሉ 11 መምህራኖቻችን የትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲስ የማወዳደሪያ መስፈርት ተመዝነው ከሌክቸረርነት ወደ ረዳት ፕሮፌሰርነት ደረጃ ያደጉ በመሆኑ ሴኔቱ የደረጃ እድገቱን ገምግሞ አፅድቋል። በደረጃ እድገቱ የተተካቱት መምህራን፦ 1ኛ. ረ/ፕ አብዱ ሰይድ ሙሃመድ2ኛ. ረ/ፕ አደም ወንድሜነህ በላይ3ኛ. ረ/ፕ አዲሱ ጌቴ ንጋቱ4ኛ. ረ/ፕ አጃናው ነገሰ5ኛ. ረ/ፕ አስማማው ደምስ ብዙነህ6ኛ. ረ/ፕ አየልኝ መንገሻ ካሴ7ኛ. ረ/ፕ ብርሃን አለምነው ታመነ8ኛ. ረ/ፕ ብሩክ በለጠው አባተ9ኛ. ረ/ፕ ጌታሁን ፈንታው ሙላው10ኛ. ረ/ፕ ጌትነት ገደፋው አዘዘ11ኛ. ረ/ፕ ሙሃመድ አህመድ ይማም ናቸወ። በመሆኑም በዛሬው እለት በጥረታችሁ የደረጃ እድገት ያገኛችሁ መምህራን በሙሉ በመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስም እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ወቅቱ ተቋማችንን መልሰን የምንገነባበት በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ጠንክራችሁ እንድትሰሩ ሀላፊነት የተጣለባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀትና በመተባበር ለተቋሙ ራዕይ እውን መሆን ተግታችሁ የምትሰሩበት ጊዜ መልካም እንዲሆን እንመኛለን። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!! ወልድያ ዩኒቨርሲቲየካቲት 3/2014 ዓ.ም