የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ ለመደገፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አገልግሎት የሚውል 1,000,000/አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን አበረከተ፡፡ ከድጋፎቹ መካከልም 10,000 ሃይላንድ ውሃ፣ፍራሽ፣አንሶላ፣ብርድልብስ፣ሩዝ፣ምስር ክክ፣ስኳር፣መመገቢያ ስሃኖችንና ኩባያወችን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎችም ይገኙበታል፡፡ዩኒቨርሲቲው በአማራ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በኩል የሚደረገውን ድጋፍም እያስተባበረ ይገኛል፡፡የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች በበኩላቸው በቀጣይ ከደመወዛቸው የሚቆረጥ ከ5-20% የሚሆን ገንዘብ ለመለገስ በገቡት ቃል መሠረት ገንዘቡን የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ 63 ዩኒት ደምም ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡