ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከል ስራ ጀመረ !

የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከል የተለያዩ አካላት በተገኙበት ሰኔ 11-2012 ዓ.ም ስራ ጀምሯል ፡፡ የማስጀመሪያ ፕሮግራሙን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን፣የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሃመድ ያሲን፣የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አበበ ግርማን ጨምሮ ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደር አካላት፣የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የምርመራ ማዕከሉ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል ፡፡