የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት በ2015 ዓ/ም በ2ኛ ዲግሪ በመደበኛ (Regular) እና ቅዳሜና እሁድ (Extension) መርሃ ግብር አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ከህዳር 20/2015 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 7/2015 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- School of Mechanical & Chemical Engineering
* MSc in Sustainable Energy engineering
* MSc in Industrial Management - School of Civil & Water Resource Engineering
* MSc in Construction Engineering and Management
* MSc in Hydraulic Engineering - School of Computing
* MSc in Information Technology
* MSc in Computer Science
አመልካቾች ለመመዝገብ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ማስረጃዎች
- የምዝገባ ማመልከቻ ክፍያ 150 ብር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ሂሳብ ቁጥር /1000023927415/ ከፍለው ለዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ የክፍያ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፤
- 3×4 የሆነ አራት /04/ ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ካርድ ፣ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪቢት ፣ የ10ኛና የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ከማይመለሰ አንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ የሚችል፤
- ኦፊሻል ትራንስክሪቢት ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ ማስላክ የሚችል፤
- በመንግስት ወጭ ለምትማሩ አመልካቾች ከመስሪያ ቤታችሁ ወይም ከሚያስተምራችሁ ተቋም የስምምነት ደብዳቤ ለምዝገባ ስትመጡ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የትምህርት ቦታ: በዋናው ግቢ
- የማመልከቻ ቦታ፡ ጀነቶ በር በሚገኘው ዋናው ግቢ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሬጅስትራር
- የማመልከቻ ጊዜ፡ ከህዳር 22- ታህሳስ 9/2015 ዓ.ም ሲሆን የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው፡ ታህሳስ 10/2015 ዓ.ም
- የትምህርት ምዝገባ፡ ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም (ለመደበኛ)፣ ታህሳስ 14/2015ዓ.ም (ለቅዳሜና እሁድ) ጀምሮ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት
- ትምህርት የሚጀመረው፡ ታህሳስ 18/2015 ዓ/ም (ለመደበኛ)፣ ታህሳስ 22/2015 ዓ.ም (ለቅዳሜና እሁድ)፤
- በተጨማሪ በተለዋዋጭ ነባራዊና አስገዳጅ ሁኔታዎች ምክንያት የሚቀየር መረጃ ካለ በዚሁ በዩኒቨርሲቲያችን ድህረ-ገጽ በማስታወቂያ የምንገልጽ ይሆናል፡፡