• Main Gate

Events Calendar

February 2019
S M T W T F S
27 28 29 30 31 1 2
3 4 5 6 7 8 9
10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23
24 25 26 27 28 1 2

Latest Events

No events

ማስታወቂያ

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ2008ዓ.ም በክረምት መርሃ-ግብር ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የቅበላ መስፈርት መሰረት በመጀመሪያ እና በ2ኛ ድግሪ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች ትምህርት ስለሚሰጥ የእድሉ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

· በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ፋካልቲ

o I . 1st Degree

§ ባዮሎጂ (Applied and/ or teaching)

§ ኬሚስትሪ (Applied and/ or teaching)

§ ፊዚክስ (Applied and/ or teaching)

§ ሒሳብ (Applied and/ or teaching)

§ ስፖርት ሳይንስ (Applied and/ or teaching)

o II. 2nd Degree

§ Mathematical Modeling

· ጤና ሳይንስ ፋኩልቲ (1st Degree)

§ አፕግሬዲ ነርሲንግ

§ አፕግሬዲ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጅ

§ አፕግሬዲ ሚድዋይፈሪ

· በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ (1st Degree)

§ አካውንቲንግ እና ፋይናነስ

§ ቢዝነስ ማኔጅመንት

§ ኢኮኖሚክስ

· ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ፋኩልቲ (1st Degree)

§ ጅኦግራፊና የአካባቢ ጥናት ትምህርት (Applied and/ or teaching)

§ አማርኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ (Applied and/ or teaching)

§ እንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ (Applied and/ or teaching)

§ ሶሽዮሎጂ (Applied)

· ስነ ትምህርትና ስነ ባህሪ ፋካልቲ

o (1st Degree)

§ ስኩልና ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂ

§ የልዩ ፍላጎት ትምህርት

§ አፕላይድ ሳይኮሎጅ

§ ፔዳጎጂካል ሳይንስ ኮምፖሲት ጂኦግራፊ

· 2nd Degree

§ MA  in Educational psychology

 

የአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የመቀበያ መስፈርት ፣

I. በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ-ግብር

ተ.ቁ

ተመዝጋቢዎች የሚያቀርቡት የት/ት ማስረጃ ዓይነት

የአዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች መቀበያ መስፈርት

በምዝገባ ወይም ማመልከቻ ወቅት መቅረብ ያለባቸው የት/ት ማስረጃዎች

1.

የከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ውጤት ኖሯቸው ለዲግሪ መርሀ-ግብር ለመማር የሚፈልጉ ተማሪዎች

የመሰናዶ ት/ት አጠናቀው  በተፈተኑበት የት/ት ዘመን ት/ት ሚኒስቴር የወሰነውን  ዝቅተኛውን  የከፍተኛ ት/ት ተቋም የመግቢያ ነጥብ ያገኙ

· የ2ኛ ደረጃ አጠቃላይ ፈተና /ከ9ኛ-10ኛ/ ውጤት

· 9ኛ-10ኛ የተማሪው ውጤት መግለጫ/ትራንስክርፒት/

· የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለፉበት የምስከር ወረቀት

· 11ኛ-12ኛ የተማሪው ውጤት መግለጫ ትራንስክርፒት

· ት/ሚ/ር የወሰነው የየዘመኑ የከፍተኛ ት/ት ተቋም መግቢያ ፈተና ውጤት

2.

በድሮው ሥርዓተ ትምህርት 12ኛ ክፍል አጠናቀው ከፍተኛ ት/ት ተቋም ገብተው በዲፕሎማ የተመረቁና ለዲግሪ መርሀ-ግብር ለመቀጠል የሚፈልጉ

· የመመረቂያ ውጤታቸው 2.00  እና በላይ የሆነ፣

· ከ9ኛ-12ኛ ክፍል የተማሪው ውጤት መግለጫ ትራንስክርፒት፣

· የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱበትና ያለፉበት የምስክር ወረቀት፣

· ከኮሌጅ የተመረቁበት ዲፕሎማ፣

· የኮሌጅ ውጤት መግለጫ/student Copy/

3

ከአሁን  በፊት የመጀመሪያ ዲግሪና በላይ ተመርቀው ያጠናቀቁና በሌላ የት/ት መስክ ለዲግሪ መርሀ-ግብር መቀጠል የሚፈልጉ፣

· የመመረቂያ ድግሪ ውጤት 2.00 እና በላይ ያላቸው፣

· የ8ኛ ክፍል የምስክር ወረቀት፣

· 9ኛ-12ኛ ክፍል የተማሪው ውጤት መግለጫ /Transcript/፣

· የከፍተኛ ት/ት ተቋም ለመግባት የሚያስችል ውጤት መግለጫ፣

· የዲግሪ/የማስተር ት/ት ማስረጃ ፣

· የከፍተኛ ት/ት ተቋም የተማሩበት የተማሪው ውጤት መግለጫ

/student Copy/፡፡

4.

እስከ 10ኛ/12ኛ ተምረው ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 እና በላይ የተመረቁ ተማሪዎች የሆኑና ዲግሪ ለመማር የሚፈልጉ

· የደረጃ አራት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣

· ዲፕሎማ

· የ8ኛ ክፍል የምስክር ወረቀት፣

· 9ኛ-10ኛ/11ኛ-12ኛ/9ኛ-12ኛ/ የተማሪው ውጤት መግለጫ/ትራንስክርፒት፣

· ደረጃ አራት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ፣

· ቢቻል አንድ ዓመት የሥራ ልምድ

5.

በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና የESLCE ውጤት ኖሯቸው ለዲግሪ መርሀ ግብር የሚቀጥሉ፣

· የESLCE ውጤት፣

· ለወንዶች 3.2 እና ለሴቶች 3.0 ያላቸው፡፡

· የ8ኛ ክፍል የምስክር ወረቀት፣

· ከ9ኛ-12ኛ ክፍል የተማሩበት የተማሪው ውጤት መግለጫ/ትራንስክርፒት/፣

· የESLCE ውጤት፡፡

6.

በመምህርነት ሙያ 10+3 የተመረቁ ና ለዲግሪ መርሀ-ግብር ስልጠና መውሰድ የሚፈልጉ

· በዲፕሎማ እውቅና ካለው ተቋም የተመረቀ/ች/

· የመመረቂያ ውጤት 2.00 ነጥብና በላይ፣

· በተመሳሳይ/ተዛማጅ የትምህርት መስክ ለመማር ፍላጎት ያላቸው

· የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለፉበት የምስክር ወረቀት፣

· ከ9ኛ-10ኛ/11ኛ-12ኛ/ከ9ኛ-12ኛ የተማሩበት የተማሪ ውጤት መግለጫ/ትራንስክርፒት፣

· ዲፕሎማ፣

· የኮሌጅ የተማሪ ውጤት መግለጫ  /student copy/፣

· በስፖንሰር የሚማሩ ከሆነ የስፖን ሰርሺፕ ደብዳቤ፣

7.

በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት በመደበኛ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በተለያየ ምክንያት አቋርጠው በዩኒቨርሲቲያችን ተከታታይ ት/ት ክፍል ት/ት ለመቀጠል የሚፈልጉ

· በት/ት ላይ የነበሩ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ፣

· የተማሪው ውጤት መግለጫ     /student copy/፡፡

· የቆዩበትን የወጭ መጋራት (cost sharing) ክፍያ መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ደረሰኘን ማቅረብ የሚችሉ

· ከነበሩበት ዩኒቨርሲቲ የዝውውር ስምምነት፣

· ውጤት ያላቸውና በመማር ላይ መሆናቸውን የሚገልፅ /official student copy/ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

ማሳሰቢያ

· ማንኛውም ማስረጃዎች ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ አያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

· በመንግስት የት/ት ተቋም በመደበኛ ፕሮግራም የሚማሩትንና በዝውውር በዩኒቨርሲቲያችን በተመሳሳይ መስክ ለመማር የሚያመልከቱ በተከታታይ / ፕሮግራም መቀበል ይቻላል፣

· ከመንግስት የት/ት ተቋም ውጪ በግል ተቋም ተምረው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተመዝጋቢ ተማሪዎች ከሚመለከተው ክፍል ዕውቅና የተሰጠው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አመልካቹ አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፣

· ከዲፕሎማ የትምህርት ዝግጅት ዲግሪ መርሀ-ግብር ለመማር ቀደም ሲል በቀጥታ ባጠናቀቁት ወይም ተመሳሳይ የት/ መስክ ብቻ ለመቀጠል ማመልከት የሚቻል ሲሆን ተመሳሳይነት በሌለው የት/ መስክ መመዝገብ አይቻልም፡፡

· ዲግሪና በላይ የት/ት ዝግጅት ያላቸው አመልካቾች በፈለጉት የት/ት መስክ ገብተው መማር ይችላሉ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች መመዝገብ ሲችሉ የማህበራዊ ሳይንስ ወደ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ መመዝገብ አይችሉም፡፡

· በ12ኛ ክፍል ውጤት ከሚመዘገቡት ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም አመልካቾች ቢቻል 1ዓመት የስራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊ እውቅና ካለው መስሪያ ቤት (ድርጅት) ማቅረብ አለባቸው፡

· በመምህርነት ሙያ የሚሰለጥኑ ተማሪዎች አፕላይድ ኮርሶችን ከወሰዱ በኋላ የፒጂዲቲ ኮርሶችን የሚወስዱ ሲሆን ካልወሰዱ ግን የሚሰጣቸው ድግሪ የአፕላይድ ብቻ ይሆናል፡፡

· II. ለድህረ ምረቃ /ለ2ኛ ዲግሪ/መርሀ-ግብር/

Ø ተመዝጋቢዎች ለማመልከት ማሟላት የሚገባቸው፡-

§ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ መመረቃቸውን የሚያሳይ ዲግሪ ኦርጅናል እና 2 ፎቶ ኮፒ የት/ ማስረጃዎች፡

§ በመንግስት መስሪያ ቤት የሚማሩ ከሆነ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፡

§ ኦፊሻል ትራንሰክሪፕት ለዩኒቨርስቲያችን ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ፖ.ሳ.ቁ 400 ማስላክ ይጠበቅባቸዋል

Ø ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መረጃዎች፡-

§ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ

Ø የክፍያ ዓይነትና መጠን (ለመጀመሪያ ድግሪና ለ2ኛ ድግሪ)

§ ለማመልከቻ ብር 30.00

§ ለመግቢያ ፈተና ብር 50.00

§ ለመመዝገቢያ ብር 50.00

· የትምህርት ክፍያ መጠን

Ø ለመጀመሪያ ድግሪ

§ በላብራቶሪ ተደግፈው ለማይሰጡ የትምህርት ዓይነቶች (ትምህርት ክፍሉ እንደሚገኝበት ፋኩልቲ ሁኔታ)

§ ከብር 80.00 እስከ ብር 100 በክሬዲት ሰዓት፤

§ በላብራቶሪ ተደግፈው ለሚሰጡ የትምህርት ዓይነቶች (ትምህርት ክፍሉ እንደሚገኝበት ፋኩልቲ ሁኔታ)

§ ከብር 90.00 እስከ ብር 125 በክሬዲት ሰዓት፤

§ የመመረቂያ ፅሁፍን ወጭ ተማሪው በሙሉ ይሸፍናል

Ø ለ2ኛ ድግሪ

§ በ1ክሬዲት ሰዓት/መጠነ ግብር ብር 500/አምስት መቶ ብር/፣

§ የመመረቂያ ፅሁፍን ወጭ ተማሪው በሙሉ ይሸፍናል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ፡- ጀነቶ በር በሚገኘው ዋና ግቢ ሬጅስትራር /ቤት

የማመልከቻ መመዝገቢያ ቀን፡- ግንቦት 24-ሰኔ 23/2008.

የመግቢያ ፈተና፡ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል

የትምህርት መመዝገቢያ ቀን፡- ሀምሌ 06-07/2008 /

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን፡- ሀምሌ 08/2008.

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር----0335400683


የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይና ርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፡፡

Last Modified Date

 November 21, 2018, 1:28 pm 

Copyright © 2014. Woldia University. All Rights Reserved.