• Dormitory Area

Events Calendar

May 2019
S M T W T F S
28 29 30 1 2 3 4
5 6 7 8 9 10 11
12 13 14 15 16 17 18
19 20 21 22 23 24 25
26 27 28 29 30 31 1

Latest Events

No events
Home Ethics and Anti-corruption

ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ወቅት ስለሚኖሯቸው መብቶች፤ሊከተሉት ስለሚገባው ሰነምግባር፤እንዲያከብሯቸው ስለሚጠበቁ ግዴታዎች፤ህግን አለማክበር ስለሚያስከትለው ተጠያቂነትና ቅጣት እንዲሁም ስለሚዳኙበት አግባብ በአጭሩ

መግቢያ

ተማሪዎች ከቤተሰብ ቁጥጥር ወጥተውና ርቀው በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የጋራ ኑሮን ሲጀምሩ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ከመኖራቸው ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ ባህል፣ ወግ እና ልማድ እንግዶች የሚሆኑበት አገጣሚ ሰፊ በመሆኑ በግቢና ከግቢ ውጭ ሊያሳዩት የሚገባውን መልካም ሰነ-ምግባር ቀድሞ ማስገንዘቡ ጠቀሚታው የጐላ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ የተማሪዎች የስነ-ስርዓት መተዳደሪያ ደንብን አውቀው በትምህርት ገበታ ላይ እስካሉ መልካም ስነ-ምግባርን በመከተል ሳይማር ያስተማራቸውን ሰፊ ህዝብ ውለታ ከፋይ መሆን ይጠበቅባቸዋል ፡፡ የዚህ ፀሁፍ መዘጋጀት ዓላማም የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች የስነ-ስርዓት ደንብ ማስገንዘብ ነው፡፡

የተማሪ መብቶች

በህገ-መንግስቱና በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 650/2001 የተዘረዘሩት መብቶች እንደተጠበቁ ሆኖ ተማሪዎች -

· ተማሪን በሚመለከቱ ጉዳዮች የመሳተፍና በዩኒቨርሲቲው አስ/ በድምፅ የመሰማት

· በዩኒቨርሲቲው በሚቀርቡ አገልግሎቶች እኩል የመጠቀም

· የወጭ መጋራት ውል እስከፈረሙ ወይም ቅድሚያ እስከከፈሉ የምግብ የምኝታ የሕክምናና የመዝናኛ አገልግሎትን የማገኘት

· የበኩላቸውን ክርክርና ማስረጃ በማቅረብ ፍትህ የማገኝትና በተገቢው አካል የመዳኝት

· በተለያዩ ክበባትና የምግብ ቤት የምኝታ የዲስኘሊን የመዝናኛ የሕክምና ....... ኮሚቴ በአባልነት የመሳተፍ

· በብሄር በፆታ በሐይማኖት ፣በፖለቲካ .. በሚመጡ ልዩነትና አድሎ የመጠበቅ

· በዩኒቨርሲቲው ህገ-ደንብ / Legislation/ የተካተቱትን ትምህርት ነክ መብቶች የመጠቀም

· የመማር፣ ጠይቆ የመረዳት የፈተና ኘሮግራም የማወቅ፣ የፈተና ውጤት የማየት፣ የትምህርት ማስረጃ የማገኝት መምህራንን የመገምገም፣ በትምህርት ጉዳይ በጋራና በፖናል ውይይት የማዘጋጀት ..... የመሳሰሉት መብቶች ይኖሯቸዋል፡፡

የተማሪ ግዴታዎች

ተማሪዎች የሚከተሉት ግዴታዎች አሏቸው -

· እያንዳንዱን የትምህርት ኮርስ/የትምህርት ዓይነት/ በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት በሌክቸር፣ በሠርቶ ማሳያ/በላቦራቶሪ/፣በቲቶሪያል ፣በሾፖችና በመስክ የመገኘትና ሁኔታው የሚጠይቀውን ተግባር የማከናወን፣

· መምህራን የሚሰጡትን የቤት ስራ፣ የመስክ ስራ፣ ፈተናዎች፣ የተለያዩ መልመጃዎችና የላቦራቶሪ ሪፖርቶች በወቅቱ አጠናቆ የማቅረብ፣

· በማንኛውም ጊዜ ትምህርት ለመጀመር በተፈቀደው የጊዜ ገደብ በዩኒቨርሲቲው በመገኘት የመመዝገብና አስፈላጊውን ፎርማሊቲ የማሟላት፣

· የሚገለገሉባቸውን የዩኒቨርሲቲውን ንብረቶችና የትምህርት መሳሪያዎች በጥንቃቄ የመያዝ፣ የመንከባከብ፣ በአግባቡ የመጠቀም እና በሰዓቱ የመመለስ፣

· የዩኒቨርሲተው አስተዳደር በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይገቡ ወይም እንዳይደርሱ ከሚከለክሏቸው ቦታዎች ራሳቸውን የማራቅ /ለምሣሌ ወንዶች በሴቶች መኝታ ቤት ሴቶችም በወንዶች መኝ ቤት ያለመገኘት

· በኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ቦታዎች፣ባልተፈቀዱ የመግቢያ በሮች ከመግባት በመኖሪያ ክፍል ውስጥ ምግብ ከማብሰል .. መቆጠብ

· ከማናቸውም ሱስ ከሚያስይዙ ጎጅ ልማዶች ራሳቸውን መጠበቅ፣

· ችግሮችን በውይይትና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍታት አላስፈላጊ ከሆኑ ከማናቸውም የጉልበተኛነት ስሜት ወይም ተግባር ራስን ማቀብ/መግታት/

· ዩኒቨርሲቲው በነፍስ ወከፍ የሚሰጣቸውን ማናቸውንም አገልግሎቶች ለሌላ ያለማስተላለፍ፣

· የመኝታ ቤትን በንጽህና መያዝና የግል ንጽህናን መጠበቅ፣

· የዩኒቨርሲቲውን የመታወቂያ ካርድ፣ የምግብ ካርድ የመያዝ አግባብነት ለው ክፍል ወይም አካል እንዲያሳዩ ሲጠየቁ የማሳየት ከዩኒቨርሲቲው በሚሰናበቱበት ጊዜ የመመለስ፣

· የወል ወይም የጋራ መገልገያዎችን የግል ያለማድረግ/ ለብቻ ያለመጠቀም/

· ማንኛውቀመም የስርቆት ተግባር ያለመፈፀም፣

· በቅጥር ግቢው ውስጥ አደገኛ መሣሪያ ይዞ አለመገኘት፣

· ማንኛውም ተማሪ በግድግዳ፣ በመስኮት ወይም ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ያለመፃፍ ወይም ያልተፈቀደ ጽሁፍ ወይም ማስታወቂያ ያለመለጠፍ፣

· በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደት የዘር፣ የሐይማኖት፣የፆታ ልዩነት የሌለበት ሁሉም በእኩልነት የሚተዳደርበት ግቢ በመሆኑ በግቢ ውስጥ ምንም አይነት የዕምነት፣ የአምልኮና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በህብረት ያለማድረግ፣

· ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲውን መመሪያዎችንና ደንቦችን የማወቅ የማክበርና የመፈፀም፣

· በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጭ መጋራት ደንብ ለትምህርትና ለአገልግሎት ተገቢውን ክፍያ የመክፈል ወይም የወጭ መጋራት ውል የመፈረም፡፡

· ከዩኒቨርሲቲው ካምፖሶች ውጭ ከህብረተሰቡ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት በመልካም

ስነ-ምግባራቸው አርአያ መሆን፡፡

· በማንኛውም ጊዜ በሴኔትና በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ክፍሎች የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን ማክበር

የስነ-ምግባር ጉድለቶችና የማስተካከያ እርምጃዎች

ተማሪዎች እንደሚያሳዩት የስነ-ምግባር ወይም ስነ-ስርዓት ጉድለቶች ክብደትና ደረጃ እንዲሁም ድግግሞሽ አኳያ እየተመዘኑ በተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የስነ ስርዓት እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ እነዚህ የስነ ስርዓት ጉድለቶችና የሚያስከትሏቸው እርምጃዎች ከዚህ ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡፡

በምክር የሚታለፉ የስነ- ምግባር ጉድለቶች

· የመመገቢያ እቃዎችን በተገቢው ቦታ ያለማስቀመጥ /ያለመመለስ/

· በጋራ የመገልገያ አካባቢዎች ማለትም በዶርሚተሪዎች በመማሪያ ክፍሎች በቤተ መፃህፍት በወርክሾፖችና በቤተሙከራ ወዘተ ከፍተኛ ድምጽ /ጩኸት/ ማሰማት ወይም ሬዲዮ /ቴኘ/ መክፈት ወይም ማስጮህ የአካባቢ ፀጥታን ማደፍረስ፣

· በመኝታ ቤት ግድግዳዎች፣ መስኮቶች፣ በሮች፣ ወዘተ ላይ መፃፍ ወይም ስዕል መለጠፍ፣

· በእጅና ፊት መታጠቢያ ቦታዎች ልብስ ማጠብ፣

· በመማሪያ ክፍሎች፣ በአዳራሾችና በአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ወንበሮችንና ጠረንጴዛዎችን ከቦታ ቦታ ማዛወር፣

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

የቃል ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶች

· በምክር የሚታለፋ የስነ-ምግባር ጉድለቶች ስር የተመለከቱትን ጥፋቶች ፈጽሞ በምክር የታለፈ ተማሪ ያንኑ ወይም ሌላ ተመሳሳይ የስነ ምግባር ጉድለት ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ሲገኝ፣

· የመኝታ ቦታን ያለፈቃድ መቀየር፣

· በመማሪያ ክፍሎች፣ በአብያተ መጻህፍት፣ በመኝታ ህንፃዎችና በሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችና ግድግዳዎች እንዲሁም በወንበሮችና ጠረንጴዛዎች ላይ መፃፍ /ስዕል መሣል/

· አግባብ ያላቸው የዩኒቨርሲቲው አካላት ወይም ኃላፊዎች የሚያወጧቸውን መመሪያዎች አለማክበር፣

· በምግብ ቤትና በሌሎችም የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ የአገልግሎት ተራን አለመጠበቅ፣

· በምግብ ቤት ውስጥ እጅን መታጠብ፣

· የግልና የጋራ ጤንነትን ሊጎዱ የሚችሉ የንጽህና ጉድለቶችን የሚያስከትሉ ተግባራትን መፈፀም፣ /በተራ ክፍል አለማጽዳት፣ አልጋ አለማንጠፍ፣ የግል ንጽህናን አለመጠበቅ፣

· ውሃና የኤሌክትሪክ ሃይል ያለአግባብ መጠቀም /ማባከን/ /ውሃ ከፍቶና መብራት አብርቶ መሄድ/

· ከመኝታ ቤትና ከሌሎች አገልግሎት ተጋሪዎች ጋር ተግባብቶና ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘት፣

· ነጠላ ጫማ ተጫምቶ፣ የሌሊት ልብስ/ ቢጃማ/ ለብሶ እና የሴትም ሆነ የወንድ የሚታዘል ፖርሳ ይዞ ወደ መመገቢያ ካፌ መግባት

· በካፌ መመገቢያ ሰዓት የሰልፍ ስነ ስርዓትን አለማክበር

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶች

· የቃል ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶችን ፈጽሞ በቃል ማስጠንቀቂያ የታለፈ ተማሪ ያንኑ ወይም ተመሳሳይ የሥነ ምግባር ጉድለት ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ሲገኝ፣

· ባልተመደበበት የመኝታ ክፍል ከሌላ ተማሪ ጋር ተዳብሎ መተኛት ወይም አስተኝቶ መገኘት

· ያለፈቃድ ምግብ ከምግብ ቤት ማውጣት ከዳቦ በስተቀር

· ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲ ንብረት በአግባቡ አለመጠቀም፣

· የተለጠፉ ህጋዊ ማስታወቂያዎችን ማንሣት፣ መቅደድ፣ መደለዝ ወይም ማበላሸት፣

· የመኝታ አገልግሎት ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው አዳብሎ ማስተኛት፣ /ተማሪ ለተማሪ/

· በመግቢያ በር፣ በምግብ ቤት፣ በአብያተ መጽሀፍት፣ በመፈተኛ ክፍል ወዘተ የመታወቂያ ካርድና ወይም የአገልግሎት መለያ ካርድ ሲጠየቅ ለማሳየት ፈቃደኛ ሆኖ አለመገኘት

· በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ጫትና መሰል አደንዛዥ እፆች ይዞ መግባት/ሲጠቀሙ መገኘት/

· ሰክሮ ወደ ግቢ መግባትና ያልተፈለገ ጩኸት ማሰማት

· ወደ ቅጥር ግቢ መግቢያ ተብሎ የተደነገገን የሰዓት ገደብ አለማክበር /ምሽት 3 ሰዓት/ ማሳለፍ

· ያልተፈቀዱ የኤሌክትሪክ እቃዎችን መጠቀም፣ በመኝታ ክፍል ውስጥ ምግብ ማብሰል፣ መመገብ፣ በምግብ ቤት ውስጥ በድጋሚ ሲመገቡና ሊመገቡ ሲመክሩ መገኘት፣

· በቅጥር ግቢው ውስጥ፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በቤተ መጽሀፍት፣ በመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች በአጠቃላይ ሰው በሚሰበሰበበት ስፍራ ሲጋራ ማጨስ፣

· በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉ አትክልቶችን መርገጥ/ መቁረጥ/

· በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፈተና ከሌላ ተማሪ መቅዳት፣ ያልተፈቀዱ ጽሁፎችንና መሣሪያዎችን ይዞ መገኘት፣በፈተና ውስጥ ሞባይል አጥፍቶ አለመገኘት፣ ይህንኑ ተላልፎ መገኘት በተደራቢነት በአካዳሚክ ኮሚሽን የሚወሰነው ቅጣት ተግባራዊ ይደረግበታል፡፡

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶችን መፈፀም፡፡

· የዩኒቨርሲው ተማሪ ያልሆነን ግለሰብ በመኝታ ክፍል ውስጥ ማስተናገድ /ማስተኛት/

ለአንድ ወሰነ ትምህርት /አንድ ሴሚስተር/ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱ ከፍተኛ ጥፋቶች፣

· የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጥፋቶች አንዱን በድጋሜ አጥፍተው ሲገኙ፣

· የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ /አባል /መምህር፣ ሠራተኛ፣ ተማሪ/ መሳደብ

ስም ማጥፋት በዛቻ ማስፈራራት፣

· የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ ካርድን ወይም የአገልግሎት መለያ ካርድን ለሌላ ግለሰብ አሳልፎ መስጠት፣

· በአጥር ዘሎ መግባት ወይም መውጣት፣

· በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ድምጽ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘነት፣

· የመኝታ ክፍልን በር፣ መስኮት ያለአግባብ ለብልሽት መዳረግ /መገንጠል/

· ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ግለሰብ ወደ ምግብ ቤት ይዞ መግባት፣

· የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶችን ፈፅሞ በተሰጠው የጽሁፍ ማሰጠንቀቂያ ሳይታረም በመጠጥ ሀይል ሰክሮ ሁካታ መፍጠር /የአካባቢ ፀጥታን ማደፍረስ/

· በማንኛውም የትምህርት ሥራ ላይ የራስ ያልሆነን ጽሁፍ ወይም የጽሁፍ ክፍል እንደራስ ሥራ አድርጎ ማቅረብ፣

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

ለአንድ የትምህርት ዓመት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱ ከባድ ጥፋቶች

· የምክር፣ የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶች ፈጽሞ በተሰጠው ምክርና ማስጠንቀቂያ ወይም ቅጣት ከመሻሻል ይልቅ ለሶስተኛ ጊዜ በተደጋጋሚ ጥፋቶችን ፈጽሞ ሲገኝ፣

· ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባል ጋር ጥል ፈጥሮ መደባደብ፣

· በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያልተፈቀደ ስብሰባ ማካሄድ፣

· አድማ ማሳደም ወይም ለማሣደም መሞከር፣

· በተቃራኒ ፆታ መኝታ ህንፃ ውስጥ ያለፈቃድ መገኘት ወይም ሁኔታዎችን አመቻችቶ ተቃራኒ ፆታን ወደ መኝታ ህንፃ ማስገባት ወይም ለማስገባት መሞከር፣

· በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሁን በሌላም ቦታ ብጥብጥና ግጭት የሚያስከትል ያልተፈቀዱ ጽሁፎችን መለጠፍ፣

· ሴትም ሆነ ወንድ ተማሪዎችን በንግግር፣ በጽሁፍ፣ በኃይል፣ ወዘተ ማስፈራራት ፣ማስቸገር፣ ማስጨነቅ፣

· ከዩኒቨርሲቲው ካምፖሶች ውጭ የዩኒቨርሲቲውን ስም ሊያጎድፍ የሚችል አስነዋሪ ተግባር ተሰማርቶ የተገኘና ለዚህም ከህጋዊ አካል ሪፖርት የቀረበበት፣

· ተገቢ ባልሆነ መንገድ መምህራንና ሠራተኞችን ከስራቸው ጋር በተያያዘ መዝለፍ፣

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

ለሁለት የትምህርት ዓመት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱ ከባድ ጥፋቶች

· በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት ስርቆት ሲፈጽም መገኘት፣

· የዩኒቨርሲቲው ንብረት የሆኑ መፃህፍት ገፆችን መቅደድ /መገንጠል/

· በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በሚሰጡ ፈተናዎች አዳራሽ ውስጥ ተገኝቶ ለሌላ ተፈታኝ ሲፈተን መገኘት፣

· በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በህግ የተከለከለ አደንዛዥ ዕጽ /Drug/ መጠቀም፣ ይዞ መገኘት፣

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲው የትምህርት መርሃ-ግብር መሰናበት /መባረርን/ የሚያስከትሉ ከፍተኛ ጥፋቶች፣

· ለአንድ ወሰነ ትምህርት ለአንድ እና ሁለት የትምህርት ዓመት ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱ የስነ ምግባር ጉድለቶች ፈጽሞ በተወሰደው የዲስኘሊን እርምጃ መሻሻል ሳያሳይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት መፈፀም

· ድምጽ ባለው ወይም በሌለው መሣሪያ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባል የሆነ ግለሰብን መጉዳት ወይም ለመጉዳት ሙከራ ማድረግ፣

· ሴት ተማሪዎችን አስገድዶ መድፈር ወይም ለመድፈር ሙከራ ማድረግ፣

· የተጭበረበረ የትምህርት መስረጃ አቅርቦ ተመዝግቦ መገኘት፣

· በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ድምጽ ያለው የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈጽም /ስትፈጽም/ መገኘት

· ፊርማን በመኮረጅ ወይም ሰነድን መደለዝ /መሰረዝ/ ማጭበርበር/ ለማጭበርበር መሞከር፣

· ተገቢውን ክፍያ ሳይፈጽም ወይም የወጭ መጋራት ውል ሳይፈርም መማር ወይም የአገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን መሞከር፣

· ሌሎች መሰል የስነ ምግባር ጉድለቶች፣

እጩ ምሩቃን የስነ-ምግባር ጉድለቶችን ፈፅው ሲገኙ የሚወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች

እጩ ምሩቃን ለሌሎች አርአያ ሆነው መገኘት የሚገባቸው ከመሆኑ አንፃር -

· የምክር የቃል፣ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከሚያሰጡ የስነ-ምግባር ጉድለቶች አንዱን ፈፅመው ሲገኙ በአንድ ሴሚስተር ከመመረቅ እንዲዘገዩ ይደረጋል

· ለአንድ ወሰነ ትምህርት ወይም ለአንድ የትምህርት ዓመት ከትምህርት ገበታ ከሚያሳግዱ የስነ-ምግባር ጉድለቶች አንዱን ፈፅመው ሲገኙ ለሁለት ተከታትይ ወሰነ-ትምህርት ማስረጃቸው ይያዛል፡፡

· ለሁለት የትምህርት ዓመት ከትምህርት ገበታ የሚያሳግዱና እስከናካቴው ከትምህርት መርሃ ግብር መባረርን ከሚያስከትሉ የስነ-ምግባር ጉድለቶች አንዱን ፈፅመው ሲገኙ ለሁለት አመት የትምህርት ማስረጃቸው ይያዛል፡፡

የዲስኘሊን ኮሚቴ አመሰራረትና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት

· በዲሰኘሊን ኮሚቴው የተማሪዎች ተወካይ አባል በመሆን ይኖራል፣

· የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርቡ ንዑሳን የዲስኘሊን ኮሚቴዎች በተማሪዎች ዲን በኩል ይቋቋማሉ፡፡

· የኮሚቴው አባል ከሳሽ ሲሆን ከተከሳሹ ተማሪ ጋር ፀብ የስጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ከተያዘው ጉዳይ ከአባልነት ይነሳል

· የኮሚቴው ምለአተ ጉባኤ ከግማሽ በላይ ሲሆን ከተገኙት አባላት ቢያንስ የተማሪዎች ተወካይ መሆን አለበት

· በተማሪ ላይ የሚቀርብ ክስ በፅሁፍ ሆኖ ለተከሳሹም እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡

· ተከሳሹ ተማሪ ክስ በደረሰው በአምሰት ቀናት ውስጥ በአካል ወይም እንደነገሩ በወኪል መልሱን በፅሁፍ በመስጠት ማስረጃ አቅርቦ የመከራከር መብት ይኖረዋል፡

· የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት ተማሪ ቅሬታዉ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እንዲታይለት በአምስት ቀናት ቅሬታውን በፅሁፍ ለዩኒቨርሲቲው ኘሬዚዳንት ያቀርባል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ኘሬዚዳንት /ሴኔት/ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

 

Last Modified Date

 May 15, 2019, 8:15 am 

Copyright © 2014. Woldia University. All Rights Reserved.