• Main Gate

Events Calendar

February 2019
S M T W T F S
27 28 29 30 31 1 2
3 4 5 6 7 8 9
10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23
24 25 26 27 28 1 2

Latest Events

No events
Home

ከይዘንን ተግባራዊ ለማድረግ ቃለ መሀላ ተፈፀመ

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ራዕዩን ለማሳካት የሚያግዙ የተለያዩ የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ለሰራተኞች የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራ ነው ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት አራት ዓመታት የመንግስትንና የትምህርት ሚኒስቴርን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የሞጁላር መማር ማስተማር ስነ-ዘዴ፣ የትምህርት ሰራዊት ግንባታ፣የዜጎች ቻርተር፣ቢፒአር፣ ቢኤስሲ እና ካይዘን የመሳሰሉ የለውጥ መሳሪያዎች ላይ ስልጠናዎችን ከመስጠት ባሻገር በተለያየ ስፋትና ጥልቀት ወደ ተግባር ተሸጋግሮ አበረታች ለውጥ በማምጣት ላይ ይገኛል ፡፡

 

 

ይሁን አንጅ በዩኒቨርሲቲው አዲስ የሚቀጠሩ ሰራተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በእጅጉ ማደጉን ተከትሎ የለወጥ ሰራዎቹን ወጥነት ባለው መንገድ አጠናክሮ ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታን የማይፈጥር መሆኑ ታምኖበት ከበላይ አመራሩ ጀምሮ እስከፈፃሚው ድረስ የሚዘልቅ የከይዘን ስልጠና በሶስት ዙር ተዘጋጅቶ ከ600 በላይ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡

የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በ12/07/08 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው DSTV አዳራሽ ሲጀምር የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ እንደተናገሩት መላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ በጋራ ያስቀመጥነውን የተቋማችንን ራዕይ ለማሳካት በምናደርገው ርብርብ ለስኬታችን አጋዥ ከሆኑት የለውጥ መሳሪያዎች መካከል አንዱ የሆነውን የከይዘን ፍልስፍና ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ ከበላይ አመራሩ ጀምሮ እስከፈፃሚው አካል ድረስ ያለው ባለድርሻ አካላት የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ ይወጣ ዘንድ ስልጠናውን ከልብ መከታተል የመጀመሪያው ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ከስልጠናው በኋላም ከፍተኛና መካከለኛ አመራርም ሆነ መላው ሰራተኞች ወደ ተግባር ተሸጋግረን ስራዎቻችን ላይ ቀጣይነት ያለውና የማያቋርጥ ለውጥ በማምጣት ፣የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ፣ ምቹና ማራኪ የስራ አካባቢን በመፍጠር ዩኒቨርሲቲያችን ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ልንፈጥር እንደሚገባ አሳስበው ስልጠናውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡


 

በ23/7/08 ዓ.ም በተዘጋጀው የስልጠና ፕሮግራም መጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት አቶ ቢሆነኝ አያሌው እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲያችን የለውጥ ጽ/ቤትን ከአቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የለውጥ ስራዎችን


እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የዚሁ አካል የሆነው የከይዘን ስልጠና በዩኒቨርሲቲው ሲዘጋጅ የተሳታፊዎች ቁጥር ካቀድናቸው ሰልጣኞች በላይ መሆኑ የስልጠናው ሂደት ውጤታማ እንደ ነበር አመልካች ነው ብለዋል፡፡አያይዘውም ስልጠናውን ብቻ መሰልጠን የመጨረሻ ግብ ባለመሆኑ ባስተሳሰባችን ተለውጠን የለውጥ ቆስቋሽ በመሆን አገልግሎት የምንሰጣቸው ተማሪዎች በእውቀት ፣ በክህሎትና በአመለካከት ውጤታማ ሆነው ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሚወጡ ተማሪዎች ጋር ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት ለመጡት አሰልጣኞች የላቀ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ሁላችንም በጋራ ፣ በቁርጠኝነት፣በአንድ ዓይነት ስሜት ፣ በተለወጠ አስተሳሰብ የከይዘንንም ሆነ ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎችን በመተግበር ወደ ተግባር እንድንገባ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ይኸነው በላይ በበኩላቸው በሃገራችን የስልጠና ችግር እንደሌለና ከይዘን ብቻ ሳይሆን ሌሎች በርካታ የስልጠና ዓይነቶች እየተሰጡ ቢሆንም ብዙዎቹ ግን የአዳራሽ ሲሳይ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ እንደሌላቸው ገልፀው እኛ ግን አስተሳሰባችንን ቀይረን ያገኘነውን አዲስ እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ፣ ስልጠናን የማምከን ችግር በመቅረፍ ለዩኒቨርሲቲያችን እድገት እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በፕሮግራሙ መጠናቀቂያ ላይ በስልጠናው መሰረት ከይዘንን ተግባራዊ ለማድረግና በቁርጠኝነት ወደተግባር ለመሸጋገር በአሰልጣኞቹ አማካኝነት ሁሉም ተሳታፊዎች እጅ ለእጅ ተያይዘው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡


 

 

 

Last Modified Date

 November 21, 2018, 1:28 pm 

Copyright © 2014. Woldia University. All Rights Reserved.